የኢትዮዽያውያን ዴሞክራቶች ድረ-ገፅEthiopian Democrats' Website

New Generation for Democracy in Ethiopia

Forums

Post Reply
Forum Home > Members Discussion > Watch the development in Egypt

stif
Member
Posts: 21

 

2 feb 2011 by stif


የቱኒዝያን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የተነሳው የግብጽ ህዝብ ያለፈውን ሳምንት ሙሉ በስልጣን ላይ ያለውን የሙባርክ መንግስት ሲያስጨንቅ ከቆየ በሁዋላ ዛሬ ፌብሩዋሪ1 ቀን 2011 በነቂስ ወጥቶ ካይሮ ከተማን አጥለቅልቆአል። የ"አንድ ሚሊዮን ሰው ሰልፍ" ይደረጋል ተብሎ በተጠበቀበት በዚህ ዕለት እጥፍ የሚሆን ሰው ሳይወጣ እንዳልቀረ የተለያዩ የዜና ማእከላት ሲዘግቡ ውለዋል።


ካይሮ፣ አሌክሳንድሬያ፣ ስዊዝና ሳናይ እንዲሁም በርካታ የግብጽ ከተሞች በዘመናት ታሪካቸው ታይቶ የማያውቅ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ በማስተናገድ ላይ ናቸው። ህዝቡ ባለፈው ሳምንት የወጣውን የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሶ በአሁኑ ሰዓት በየአደባበዩና መንገዱ ተሳባስቦ  የሁስኒ ሙበራክን ከስልጣን መውረድ በመጠየቅ ላይ ይገኛል።


ሙባረክ ከአገር ካልወጣ፣ ቤት አልገባም ነው ህዝቡ የሚለው። ሙባራክ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ለሽግግር መንግስት ከማስረከብ በታች የሚቀርብ ማንኛውንም መሸንገያ ህዝቡ እንደማይቀበል ግልጽ አድርጎአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሙባራክ ባደረጉት ንግግር...

       "ለነጻነትዋና ለክብርዋ ስዋደቅላት የነበርኩላት  ምድር ላይ ህይወቴ ያልፋል እንጂ አገሬን ለቅቄ አልሄድም።" ብለዋል። ሙባረክ  በመስከረሙ ምርጫ  እንደማይሳተፉና የስልጣን ዘመናቸው እስኪያበቃ ግን አስፈላጊውን ማሻሻያ እያደረጉ እንደሚቆዩ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ ህዝቡ ሙባራክን እስከ መስከረም የመጠበቅ ትዕግስት በፍጹም እንደሌለው ከዛሬው ሰልፍ መገንዘብ አያስቸግርም።


የግብጽ ጦር ሃይል ቀደም ሲል በህዝቡ ላይ ምንም አይነት እርምጃ የማይወስድ መሆኑንና  በጎዳናዎች የሚወጣው የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ብቻ መሆኑን በማስታወቅ በዚህ ፍጥጫ መሃል በታሪክ የማይወቀስበትን አቁዋም መርጦአል። ሰሞኑን ሰልፈኛውን ሲያዋክብ የሰነበተው ህዝባዊ አመጽ በታኝ የጸጥታ ሃይሉ ዛሬ አደባባይ ዝር አላለም። በምትኩ ህዝቡ በተለያዩ ንኡስ የጥበቃ  ቡድኖች  ተደራጅቶ  አስደናቂ  የጥበቃ ስራ እያካሄደ ሲሆን ይህን አመጽ በዋናነት ይመራል የሚባል ተለይቶ የሚታይ ሆነ መታይት የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ  እስካሁን ብቅ አለማለቱ አመጹ ሙሉ በሙሉ በህዝብ ተነሰሽነት እንጂ ሙባረክ እንደጠቆሙት በውጭ ሃይል ወይም የተለየ አላማ ያለው ቡድን የገፋፋው እንዳልሆነ የሚያመለክት ነው። አመጹ ሃብታም ደሃውን፣ ተማሪ ሰራተኛውን፣ ሙስሊም ክርስቲያኑን ያቀፈ ሲሆን ከእድሜ ክልል አንጻር በቁጥር በዝቶ የሚታየው ሙባራክ ስልጣን ላይ ከወጡ በሁዋላ የተወለደው ወጣቱ ትውልድ ነው።


አለም በጣም ተለውጣለች። በሙበረክ ጊዜ የነበረች የቱዩብና ትራንዚስተር ቴክኖሎጂ አለም ታሪክ ማህደር ውስጥ ከገባች አመታት ተቆጥረዋ። አሁን ዲጂታል ቴክኖሎጂ አለማችንን አንድ መንደር አድርጎአታል። በኢንተርኔትና በሴልፎን አማካይነት መልእከትና መረጃ በቅጽበት ማስተላለፍ ተችሎአል። በአካል መገናኘት በማይቻልበት ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በፌስቡክና ትዊቴር ተገናኝተው ይወያያሉ፣ ይማከራሉ፣ ይቀጣጠራሉ። ይህን ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ትውፊት በአብዘኛው የሚጠቀምበት አዲሱ ትውልድ ነው። እነሙባረክ ስልጣን ላይ ከወጡ በሁዋላ የተወለደው ትውልድ።


በግብጽ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም አገር ያለው ይህ አዲስ ትውልድ ለውጥ ይፈልጋል።  ባረጀና ባፈጅው የሀምሰና ስልሳ ዓ ም የፖለቲካ አስተሰሰብ የሚመራበት ጊዜ ማክተሙን፣ ለግብጽ ህዝባዊ አመጹ መንሳሳት ከፍተኛ ሚና የተጫወተ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ራሱ ያበስራል። የነማርክስ የላባደር ዲሞክራሲ፣ የነማኦ ዲሞክራሲየዊ አብዮት፣ የስታሊን የብሄር ጥያቄ አፈታት ቦታቸው እንደ ትራንዚስተር ሙዚየም ውስጥ ነው። አይሰሩም። ስለማይሰሩ ወጣቱ አይቀበላቸውም። ወጣቱ ያለተቀበለው ነገር ደግሞ በወቅቱ ገለል ካላለ ውሎ አድሮ በህዝብ አመጽ ይገለላል።


የአፍሪካና የመካከልኛው ምስራቅ አገሮች መንግስታት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የጦርና የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የነዚህ ሃገራት ህዝብ ከግብጽ ህዝባዊ አመጽ መንስኤ፣ ሂደትና የችግሩ አፈታት የሚማሩት ብዙ ነገሮች ስለሚኖር በጥሞና መከታተሉ ይበጃል።


ስቲፍ/  

 

 


February 1, 2011 at 8:41 PM Flag Quote & Reply

You must login to post.

Share on Facebook

Share on Facebook

The Weather Channel

Quote of the Day

Quote of the Day