| Forum Home > Members Discussion > discussion about election result and EDP's response | ||
|---|---|---|
|
Member Posts: 24 |
I wrote this short message in response to a person who has a nick name "weyanew lehager" I thought it is an interesting issue to discuss about. what do you think?
ለውይይት ስለጋበዝከኝ አመሰግንሀለሁ:: በርግጥ የኢዴፓ አንድም ተመራጭ ሊያሸንፍ ባለመቻሉ ከደገረሰብኝ ድንጋጤ ገና አላገገምኩም:: ለማንኛውም ብተቃዋሚዎች ላይ ያደረግከው ትችት በተወሰነ መልኩ እውነታነት ቢኖረውም ብዙ የማልስማማበት ጉዳይ አለ:: በምስማማበት ልጀምር የኢህአዴግ ጠንካራ ድርጅት መሆንን እስማማበታለሁ:: የአብዛኞቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች ደካማ መሆንን እስማማበታለሁ:: በተወሰነ ደረጃ ግለሰቦች ላይ የመንጠልጠላ ባህሪ በተቃዋሚው በኩል እንዳለ እስማማለሁ:: ኢህአዴግ ያለውን ድርጅታዊ ብቃት እንዲገፋበት ተቃዋሚዎችም ደካማ ጎናቸውን እንዲያሻሽሉ እመኛለሁ:: በተለይ ተባብሮ የመጠናከር ጉዳይ በሰፊው ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው:: የማልስማማባቸውን ደግሞ ላንሳ:: በመጀመሪያ ኢዴፓና መድረክ ፕሮግራማቸው አይመሳሰልም:: ሲጀምር መድረክ የሚባለው ስብስብ ፕሮግራም የለውም:: በውስጡ ያሉ ግለሰቦችን አንጋፋነት ግምት ውስጥ በማስገባት እንዴት ፕሮግራም የላቸውም ትላለህ ትል ይሆናል:: ሆኖም አመለካከታቸው አራምባናቆቦ የሆኑ ሰዎች በመሆናቸው የጋራ ፕሮግራም ሊኖራቸውም አይችልም:: መለስተኛ ፕሮግራም የሚሉት መሰረታዊዎችን ጥያቄዎች የመለሰ ስላልሆነ ከቁምነገር የሚቆጠር ሊሆን አይችልም:: በተረፈ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መካካል የሚታየው የግል ጠብ በጣም አሳፋሪ ነው:: ወደ ኢዴፓ ስንመጣ ትንሽ የተሟላ መረጃ እጥረት እንዳለብህ እገምታለሁ:: በመጀመሪያ አቶ ልደቱ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት የሆኑት ላለፉት አራት አመታት ብቻ ነው:: እንደነ መራራ ጉዲናና በየነ ዼጥሮስ ስልጣን ላይ ፊጥ ብለው ሀያ አመት አልቆዩም:: ሁለተኛ ኢዴፓ በህብረትና በጥምረት ዙሪያ ከሌሎቹ በተለየ ስኬታማ ታሪክ ያለው መሆኑ ነው:: በዚህም የመረጃ እጥረት ያለብህ ይመስለኛል:: ኢዴፓ ከቅንጅት በፊት አራት ፓርቲዎችን በመሰብሰብ በሂደት ውህደት በመፈጸም ጠንካራ ድርጅታዊና ፖለቲካዊ ብቃት መፍጠር የቻለ ፓርቲ ነው:: ሆኖም ቅንጅቱ ውስጥ በመገባት በየዋህነት በሰራው ስህተት ምክኒያት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሶበታል:: አሁን ምናልባት አንተ የማታውቀው ነገር (እንድታውቀውም አይጠበቅም ስለሆነም ባጠቃላይ መልኩ ኢዴፓ ዋና ዋና ግቦቹን ያሳካ ሲሆን ለሚቀጥለው ትግሉ መሰረትን ጥሏል:: ይህን ካልኩህ ዘንዳ በምርጫው ምነው ማሸነፍ ተሳነው ካልከኝ ምክኒያቶቹን በሶስት መክፈል ይቻላል:: አንድ ኢህአዴግ ባለፉት አምስት አመታት ባሳየው እመርታ ደጋፊዎቹ ስለጨመሩ ነው:: ሁለት ተቃዋሚዎች ባለባቸው ድክመት በተለይም በሚያሳዩት የክፍፍልና የጥላቻ ባህሪ ህዝቡ ስላዘነባቸው ነው:: በተለይ በከተሞች ኢህአዴግን የማይደግፈውን ህዝብ ብዛት ለብዙ ስለሚከፋፈሉት ለመሸነፋቸው ዋነኛ ምክኒያት ሆኗል:: ሶስት ኢህአዴግ ህዝቡን በማስገደድና በማፈን ባደረገው ተጽእኖ ህዝቡን እያስፈራራ እንዲመርጠው በማድረጉ ነው:: ለዚህ ዋነኛው ማስረጃ አቶ ልደቱ የተሸነፉበት ሁኔታ ነው:: አቶ ልደቱ በተወዳደሩበት ላሊበላና አካባቢው የተለጠፉት ውጤቶች የሚያሳዩት በላሊበላ ከተማ ሙሉ በሙሉ አቶ ልደቱ ሲያሸንፉ ማንም ሊታዘብና ሊቆጣጠር በማይችልበት በገጠር ግን ተሸንፈዋል:: በዚያ ላይ አንድ የኢህአዴግ አባል አምስት ግለሰቦችን ይዞ እየሄደ እያስገደደ የሚያስመርጥበት ሁኔታም ነበር:: ባጠቃላይ የተፈጠረው ሁኔታ አገሪቱን ወደጥሩ አቅጣጫ የሚመራ ሳይሆን የባሰ መካረርን እየፈጠረ የሚሄድ አደገኛ አካሄድ ነው:: ኢዴፓ ግን ይህ መካረር እንዳይፈጠርና አገሪቱ ወደመልካም አቅጣጫ እንድትሄድ በተቻለው መጠን እደሚሰራና በሚቀጥለው ምርጫ ግን ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ እንደሚቀርን አረጋግጥልሀለሁ:: ወንድምህ ቴዎድሮስ ሳልሳዊ | |
| ||
|
Member Posts: 1 |
I have some hting to say to all true EDP semmbers. Infact I am not a member of EDP but I prefer the party for various reason. The thing I wana say is, why we didn't oppose the human rights if it is found to be appropriate by the head emmbers of the party. I think EPDRF using this situation to show how much supports gained and to put a physicological presser which exepcted to persuade the peoples of ethiopia that the ellection process was perfect. So the only way to show the people how much EDP supporties are there beside with him just to make peacefull SELAMAWISELF. WHAT ARE YOU gays THINKING?
| |
|
-- harobiya
| ||