የኢትዮዽያውያን ዴሞክራቶች ድረ-ገፅEthiopian Democrats' Website

New Generation for Democracy in Ethiopia

Forums

Post Reply
Forum Home > Election 2010 > Words of Peace (Amharic)

stif
Member
Posts: 21

ቸር ቸሩን ያሰማን

ኢዴፓና ደጋፊዎቹ የምርጫ ስነምግባሩን ደንብ ሳይጥሱ የምርጫ ዘመቻውን በሰላም በማጠናቀቃቸው የተሰማኝን ደሰታ መግለጽ እወዳለሁ። አገራችን ገና ጀማሪ ዲሞክራሲ እንደመሆንዋ መጠን ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ይሆናል ብሎ መጠበቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን አላዋቂነትም ነው። በመሆኑም ሁሉም ፓርቲዎች ጥቃቅኑን እንከን የጀማሪነት ባህሪ መሆኑን አገናዝበው በመተው፣ ከበድ ያለውን ጥፋት ደግሞ ወደ ህግ ግቢ በመውሰድ መማማሪያ እንዲሆነን በማድረግ ዘመቻውን እንደ ኢዴፓ በሰላም እንዲያጠናቅቁ እመኝላቸዋለሁ።

ከምርጫው በሁዋላ ያለውም ሁኔታ እንዲሁ በሰላም ተጠናቅቆ የአሸናፊውን መንግስታዊ ስልጣን በውዴታ የመቀበል ድፍረቱና ባህሪው እንዲኖረን ይገባል። ያለፈው ምርጫ የተወው ጠባሳ ቀላል አይደለም። የሰዎች ህይወት ጠፍቶአል። በዚያ ቀውስ ሌጠፉት ሰዎች ህይወት አክብሮት የምናሳየው፣ ዛሬ በማንኘውም ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት እንዳይጠፋ ማድረግ ስንችል ብቻ ነው።

ከአንዳንድ አካበቢ የሚደመጡ ረባሽ አመለካከቶች አሉ። ምርጨው ከወዲሁ ተጭበርብሮአል የሚሉም ተሰምተዋል። ቦይኮት እናድርግ የሚሉም አልጠፉም። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ግን ያው ኢዴፓ ደጋግሞ እንድሚለው ዜሮ ነው። ምርጫ ዛሬ ይጭበርበር፣ ኮሮጆም ይሰረቅ፣ ዳኛውም ያድላ፣ ስልጠኑም በአናሳው እጅ ይቆይ፣ አርቀን ካየን በእያንዳንዱን የምርጫ ዘመን ጥሩ ልምድ እየገበየን እና አዲስ ትውልድ እየተተካ ስለምንሰግር አንድ ቀን በዴሞክራሲ የዳበሩትጋር እኩል እንደምንሰለፍ ማመን ይኖርብናል። አልያ ጎዳናው ጥምዝምዝ ብቻ ሳይሆን ደምም የሚያስከፍል፣ መዳረሸውም የማይታወቅ ስለሚሆን ያቺን ቀን እኛም መጪዎቹም ትውልዶች እንደናፈቅናት እንቀራለን።

ቸር ያሰማን።

ስቲፍ።

May 20, 2010 at 5:25 PM Flag Quote & Reply

You must login to post.

Share on Facebook

Share on Facebook

The Weather Channel

Quote of the Day

Quote of the Day